In 90 words
በሚጽፉት ነገር በሁሉም አልስማማም። በአንዳንድ ነገሮች ላይ ከእነሱ የተለየ አቋም ነው ያለኝ። ነገር ግን በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ሕግ አክብረው በሰላማዊ መንገድ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያደርጉ የነበረውን ነገር ሁሉ አከብራለው። ከራሳቸው አልፈው ሁሉም ዜጎች ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብታቸው ተከብሮ በሀገራቸው ጉዳይ የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ በከፈቱት ገጽ ላይ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ነበር። ለሀገራቸው ስለሚያገባቸው በብዕራቸው ሀሳባቸውን ገለጹ። ይሄ አካሄዳቸው በሶሻል ሚዲያ ውስጥ በሚሳተፉ ወጣቶች ላይ መነቃቃትን ፈጠረ። ይሄም በአምባ-ገነኖች ስላልተወደደ" በሽብርተኝነት" ከሰሷቸው። ጋዜጠኞችም ሙያቸውን አክብረው የሚንቀሳቀሱና የሚዘግቡ ስለነበር ለኢህአዴግ አልተመቹትም። ስለዚህ በተለመደው መልኩ አሰራቸው። ለኔ ሁሉም ሰላማዊ ዜጎች፣ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች እንጂ ሽብርተኞች አይደሉም።
Abenezer B. Yisihak
ምናባዊ ጨዋታ ከማሂና ከኤዶም ጋር #InMorethan90Words
እቴ'ሜቴ የፍትህ ጣዕም የፍቅር ሽታ፣
ቅኔሽ ያልገባው ያሰረሽ ሎሌ ምን አለሽ ማታ?
***
"ኧረ ብዙ ብዙ ነው ያለኝ፣
ከየት ጀምሬ ስንቱን ልንገርህ
እንዲያው ቢቀለኝ?"
ኧረ ንገሪኝ አንቺ የእውነት ቀለም
አንቺ የእውነት ፀዳል፣
ምንም ባያምን ፡ አይሰማው የለ
ያደለን ጆሮ ፣ መች ከቶ ይሞላል።
***
"አገሬን ብዬ ወገኔን ብዬ ከዜጎች ማዕድ
ከስፍራው ብገኝ፣
በቅጥፈት ዶሴ ችሎት ሰይሞ ወህኒ ዶለኝ።
ሀገሬ አድማስ ላይ እውነት ታስራ ፍትህ ጎድሎ
ፍትህ ጎድሎ፣
ወገን ተክዟል በጨካኝ በትር ልቡ ዝሎ
ልቡ ዝሎ፣
ህመሙ ያማል ጩኸቱ ይሰማል ወዲያ ርቆ
ወዲያ ርቆ፣
ከነጎድጓድ ድምፅ በእጥፍ ደምቆ
በእጥፍ ደምቆ።"
***
እኔን ይመመኝ ይመመኝ፣
እንባሽን አባሽ ሳቅሽን መላሽ ያድርገኝ
ያድርገኝ፣
የጠጣሽውን የእውነትን ጽዋ ያስጠጣኝ
ያስጠጣኝ።
የእውነት ጽዋ መራራ ነው
መራራ ነው፣
መፍለቂያ ምንጩ የህሊና ተራራ ነው
ተራራ ነው።
ተራራ ልወጣ ማዶ ልሻገር ላልመለስ
ላልመለስ፣
ያገሬ ልጆች በሞሉበት
በቁንጫ ቄስ ከሚቀደስ
ከሚቀደስ።
መርዙን ላስተፋው ያንን ክፉ
ያንን ክፉ፣
ንቅሳቱ በሚያታልል መንታ ምላስ ወገኖቼ እንዳይጠፉ
እንዳይጠፉ።
የአዞ እንባ ከሚያነባ ልጠብቅሽ
ልጠብቅሽ፣
ለከፈልሽው ውድ ዋጋ ምኔን ልስጥሽ
ምኔን ልስጥሽ??
ሐምሌ 16/2006 ማንችስተር ከተማ ሀገረ እንግሊዝ
"ኧረ ብዙ ብዙ ነው ያለኝ፣
ከየት ጀምሬ ስንቱን ልንገርህ
እንዲያው ቢቀለኝ?"
ኧረ ንገሪኝ አንቺ የእውነት ቀለም
አንቺ የእውነት ፀዳል፣
ምንም ባያምን ፡ አይሰማው የለ
ያደለን ጆሮ ፣ መች ከቶ ይሞላል።
***
"አገሬን ብዬ ወገኔን ብዬ ከዜጎች ማዕድ
ከስፍራው ብገኝ፣
በቅጥፈት ዶሴ ችሎት ሰይሞ ወህኒ ዶለኝ።
ሀገሬ አድማስ ላይ እውነት ታስራ ፍትህ ጎድሎ
ፍትህ ጎድሎ፣
ወገን ተክዟል በጨካኝ በትር ልቡ ዝሎ
ልቡ ዝሎ፣
ህመሙ ያማል ጩኸቱ ይሰማል ወዲያ ርቆ
ወዲያ ርቆ፣
ከነጎድጓድ ድምፅ በእጥፍ ደምቆ
በእጥፍ ደምቆ።"
***
እኔን ይመመኝ ይመመኝ፣
እንባሽን አባሽ ሳቅሽን መላሽ ያድርገኝ
ያድርገኝ፣
የጠጣሽውን የእውነትን ጽዋ ያስጠጣኝ
ያስጠጣኝ።
የእውነት ጽዋ መራራ ነው
መራራ ነው፣
መፍለቂያ ምንጩ የህሊና ተራራ ነው
ተራራ ነው።
ተራራ ልወጣ ማዶ ልሻገር ላልመለስ
ላልመለስ፣
ያገሬ ልጆች በሞሉበት
በቁንጫ ቄስ ከሚቀደስ
ከሚቀደስ።
መርዙን ላስተፋው ያንን ክፉ
ያንን ክፉ፣
ንቅሳቱ በሚያታልል መንታ ምላስ ወገኖቼ እንዳይጠፉ
እንዳይጠፉ።
የአዞ እንባ ከሚያነባ ልጠብቅሽ
ልጠብቅሽ፣
ለከፈልሽው ውድ ዋጋ ምኔን ልስጥሽ
ምኔን ልስጥሽ??
ሐምሌ 16/2006 ማንችስተር ከተማ ሀገረ እንግሊዝ
ተስፋለም ሆይ! ስላንተ ምን ልናገር? ስለልጅነትህ?! (ከ-ኤልያስ ገብሩ)
ሚያዚያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ንጋት ላይ ትንሿ ስልኬ አንጫረረጭ፡፡ ከእንቅልፌ ብንን ብዬ ስልኬን
ተመለከትኩት፡፡ የደወለው ወዳጄከዚህ ቀደም በዚህ ሰዓት ደውሎልኝ አያውቅም ነበር፡፡ ስልኩን ሳላነሳው ‹‹ምን
አንዳች ነገር ተፈጥሮ ይሆን?›› ብዬ ማሰላለሌን ተያያዝኩት፡፡ ከ20 ደቂቃ በኋላ ስልኩ በድጋሚ ተደወለ፣
አነሳሁት፡፡ ከደዋዩ ወዳጄጋርም ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ ‹‹ጓደኞችህ ታሰሩ አይደል?›› አለኝ፡፡ ‹‹እነማን?››
በማለት በችኮላ መለስኩለት፡፡ ‹‹ተስፋለም፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ዞን ዘጠኞች…›› ደንግጬ መረጃው እንደለሌለኝ
ነገርኩት፡፡ …ተስፋለም ከመታሰሩ ሁለት ቀናት በፊት ደውሎ ከሥራ ጋር የተገናኘ መረጃ ጠይቆኝ ነበር፡፡
ያለ ወትሮ ስልክ ሲደወል በተቻለ አቅም እረጋ ብሎ ማሰላለሰልን ከተሞክሮ ተምሬያለሁ፡፡ የቀድሞ የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን ከኢትዮጵያ መሰደድ ንጋትላይ ‹‹አለቃችሁ ተሰደደ አይደል?›› ብሎ የነገረኝ፣ እስከአሁን ድረስ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩ በጣም የገረመኝ፣ የማከብረው እና የምወደው የልጅነት ጓደኛዬ እና ወንድሜ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ነበር፡፡ እንደአንድ ነጻ እና ጎበዝ ጋዜጠኛ ለመረጃ ያለውን ቅርበት ተመልከቱ!
የሌሎቹም የጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ የጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ (በፍቄ)፣ የጦማሪያኑ የማህሌት ፋንታሁን፣ የአጥናፍ ብርሃኔ፣ የዘላለም ክብረት፣ የናትናኤል ፈለቀ፣ የአቤል ዋበላና የኤዶም ካሳዬ መሰል እስርም እጅግ አሳዝኖኛል፡፡ ዋይ! ሀገሬ!
ከተስፋለም ወልደየስ ጋር ትውውቃችን ከለጋ አፍላ ዕድሜያችን ይጀምራል፡፡ ወላጆቹ ጦላይ ወታደራዊ ካምፕን ለቅቀው አዲስ አበባ መኖር ከጀመሩ በኋላ ማለት ነው፡፡ ዛሬ በሕይወት የሌሉት የተስፍሽ ወላጅ እናት ወ/ሮ አበበች አክስት ከወላጅ አባቴ ጋር በጣም የቅርብቤተሰባዊ ትስስር አላቸው፡፡ ወ/ሮ አበበች እና አክስታቸው ለረዥም ዓመታት ልደታ መኮንኖች ክበብ አቅራቢያ አንድ ግቢ ውስጥ ኖረዋል፡፡
ዛሬ በሕይወት የሌሉት ወላጅ አባቱ እና እናቱ እንዲሁም አሁን ላይ በቅርቡ ያለችው እህቱ ራሄል ተስፋለምን ‹‹አቡሽ/አቡሼ›› በማለት ነበር ፍቅራቸውን በመግለጽ የሚጠሩት፡፡ እኔም እስከቅርብ ዓመታት ድረስ ‹‹አቡሽ›› ነበር የምለው፡፡
ከተስፋለም ጋር አብሮ በመሆን በነበሩን አጋጣሚዎች ሁሉ በጣም ደስ የሚል ጨዋታ፣ እያወጉ ረዥም ወክ የማድረግ ተደጋጋሚ ልምድናእውቀት የመካፈልየቁም ነገር ጊዜያቶችን በልጅነታችን በደንብ አጣጥመን አሳልፈናል፡፡ …እነዚህ መቼም አይደገሙ! ትዝታ ሆነው አልፈዋል፡፡ ተስፋለም አዲስ ነገር ለማወቅ እና አዲስ ነገርን ለመንካት ያለውን ጉጉት እና ትጋት ወደር የለውም፡፡ አከባቢያዊ፣ ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ መረጃዎችን ከአቅሙ በላይ ለማወቅ ይታትር ነበር፡፡ ለዕውቀት እና ለመረጃ የነበረውም የተንቀለቀ ስሜት እና ጥማትየላቀ ነው፡፡ ለዚህ ይሆን፣በብዙዎች ዘንድ በኢትዮጵያ የፕሬስ ታሪክ ትልቅ ተምሳሌት ከነበረችው የ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ መስራቾች መካከል አንዱ የሆነው?
ተስፋለምን ልጅነት ካወኩት ጊዜ አንስቶ የንባብ ቀበኛ ነው፡፡ ገበያ ላይ ያሉ መጽሐፍትን፣ ጋዜጦችንና መጽሄቶችን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከሰዎች ይዋሳል፣ ያነብባል፣ ይገዛል፣ አደራጅቶ በጥንቃቄ ያስቀምጣል፡፡ ለምሳሌ፣ ሆሊውድ ጋዜጣ እና ኢንፎቴይንመንት መጽሄትለአንባቢያን ቀርበው ህትመታቸው እስከተቋረጠባቸውጊዜያት ድረስ ያሉትን ቅጾች በተስፋለም ቤት አሁንም ድረስ በክብር ተቀምጠው ያገኟቸዋል፡፡ የሬዲዮ እና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችንበሚያስገርምመልኩ በአንክሮ ይከታተላል፡፡ ፊልሞችንም እንደዚሁ፡፡ የተመለከታቸውን ፊልሞች መቼ እንደተመለከታቸውጠቅሶ ከነዕርሶቻቸው ማስቀመጥም ልምዱ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ምን እንዳደረጋቸው ባላውቅም በርካታ ግጥሞችንም ይጽፍ ነበር፡፡ ግለ-ሀሳቡንም ይጽፋል፡፡
ተስፋለም፣ የጋዜጠኝነት ሙያን መማር ጥልቅ ፍላጎቱ መሆኑንለወላጆቹ ተናግሮ ካሳመነ በኋላ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ጋር በሚገኘው በቀድሞ የማስሚዲያ ማሰልጠኛ ኤጀንሲ የጋዜጠኝነትትምህርትን ለመመዝገብ የሄደው ከእኔ ጋር ነበር፡፡ …ከዚህ መደበኛ ትምህርት ባሻገር በሂደት ሙያውን በራሱ ጥረት ለማሻሻል ጥረቱ ትልቅ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የፍሪላንስ ሥራን በጎን በመጀመሩ ምክንያት እና በትምህርት ጥናት የተነሳ አምሽቶ ከእኩለ ሌሊት በኋላወደቤት መግባትን ልምድ አድርጎም ነበር፡፡በዚህ ወቅት በመኖሪያ ቤቶቹ ግቢ ውስጥ በጣም አምሽቶ የሚገባው ተስፋለም ነው፡፡ ተስፋለም ‹‹ለእውነተኛ ጋዜጠኝነት የተፈጠረ›› ብል አፌን ሞልቼ ነው፡፡ ሙሉ ሕይወቱን ለጋዜጠኝት ሙያ ስለመስጠቱም ሆነ ስለጥንቃቄውእመሰክራለሁ፡፡
አሁን ላይ ቀን እና ዓመተምህረቱን ዘንግቼዋለሁ፡፡ ወላጅ አባቱ ለረዥም ወራት እያመማቸው እና እየተሸላቸው ከቆዩበኋላአመሻሽ ላይ ሕይወታቸው አለፈ፡፡ በቦታውም ነበርኩ፡፡ ተስፋለም ግን ከነፍሱ ለሚወደው ሙያ ሌሊቱን ሙሉ ሲሰራ አድሮ ንጋት ላይ ወደቤቱ ሊገባ የአጥሩንበር ሲከፍት መኖሪያ ቤታቸው በሰዎች ተከብቧል፡፡ ድንጋጤው ፊቱ ላይ በግልጽ ያስታውቅበት ነበር፡፡ ማንምም ሳያናግር ወደቤቱ ዘለቀ፡፡ በጥልቅ የሚወዳቸው እና የሚሳሱለትየወላጅ አባቱ ሞት እውነት መሆኑን ተረዳ፡፡ ፊቱ ተቀያየረ፣ ግራ ተጋባ፣ አይኖቹ በዕንባ ተሞሉ፣ የአባቱን መሪር ሀዘን …
ከደቡብ ዩኒቨርሲቲ በደን ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ከተመረኩኝ በኋላ አንድ ቀን አመሻሽ ላይ ከተስፋለም ጋር ከልደታ ተነስተን ወደቦሌ መስመር ወክ በማድረግ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይበተመስጦ እያወጋን ነበር፡፡ አስታውሳለሁ፣ ወሎ ሰፈር ጋር አንድ ጥያቄ ጠየኩት፡፡ ‹‹በተማርኩት ትምህርት ደስተኛ ብሆንም ነፍሴ ግን አልረካችም›› አልኩት፡፡ ‹‹ኤልያስ ውስጥህን በእርጋታ አዳምጠው›› በማለት ተስፋለም መለሰልኝ፡፡ እውነቱን ለመናገር ውስጥን ማዳመጥ ምን ማለት እንደሆነ እስከዚያች ቅጽበት ድረስ አላውቅም ነበር፡፡ ዛሬ ከነፍሴ በምወደው የጋዜጠኝነት ሙያ ላይ እንድገኝ ‹‹…ውስጥህን አዳምጠው›› የሚለው የተስፋለም ወንድማዊ ምክር እጅጉን እንደጠቀመኝ ዛሬ ላይ ተነፈስኩት፡፡ ተስፍሽ አስተዋይ የሆነ የትንሽ ትልቅ ነበር፡፡
ተስፍሽ፣ ድንገተኛ እስርህ አመመኝ፣ ቁጭት ፈጠረብኝ፡፡ ዛሬም ድረስ ውስጤን እያንገበገበው ይገኛል፡፡ ሆኖም እሰሩ የዜጎችን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ሕገ-መንግስታዊም ሆነ ዓለማቀፋዊ መብት እንዲከበር ለምወደው ሙያ ይበልጥ በጽኑ እንድቆም ጤናማ እልህ አቀጣጥሎብኛል፡፡ የእናንተ እስርም በነጻው ፕሬስ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ጋዜጠኞችን ልብ በሃዘን ነክቷል፣ ንዴታዊ ስሜት ውስጥም ከትቷል፡፡ በጋዜጠኝነት ለመስራት ‹‹ሙያው አስጠላን›› ያሉኝም አሉ - መፍትሄ ባይሆንም፡፡
በአዲስ አበባ አራዳ ፍርድ ቤት የጓደኞችህን እና የአንተን ሁለት እጅችህ በብረት ካቴና ተጠፍንገው ስመለከት ደግሞ በመንግሥታችን እጅጉን አዘንኩ፡፡ ጠረጼዛ ላይ ያሉ ጋዜጦችን፣ መጽሄቶችንና መጽሐፍቶችን እንኳን ከልጅነትህ ጀምሮ ማዝረክረክ የማትወደው ልጅ ከነፍስህ የምትወዳትን እምዬ ኢትዮጵያን ከሙያ አጋሮችህ ጋርበሽብር እና በአመጽ ለማተራምስ ተንቀሳቅሰሃል ብዬ ለሰከንድ እኩሌታ እንኳን በጭራሽ አላስብም፡፡ለምትወደው ሙያህ ዘወትር ሚዛናዊ ዘገባን ለማቅረብ መታተርህ መንግሥት ላይ ስጋት ፈጥሮ ይሆን እንዴ? …በእናንተ ላይ የሚቀርበውን ክስ ለማወቅ በጣም የጓጓሁትምለዚሁ ነው፡፡
አይደለም ከልጅነቴ ጀምሮ በደንብ የማውቀውን ተስፋለምን ቀርቶ ሌሎች የታሰሩት የሙያ አጋሮቻችንእንኳን በሚወዷት ሀገር ላይ ሽብር እና አመጽ ለማካሄድ የማሴርዓላማ እና ዕቅድ አላቸው ብዬ ለማሰብ ፍጹም እቸገራለሁ፣ይህ የግሌ እምነት ነው፡፡
…ተስፋለምን ለረዥም ዓመታት ከማውቀው አኳያ ብዙ ማለት ብችልምለዛሬ የልጅነት ሕይወቱን ብቻ ጠቅሼ ለማለፍ ወደድኩ፡፡ተስፍሽ፣ ንጽሕናህ እና ሙያዊ ጥንቃቄህ ነጻ ያወጣሃል!!! ነገር ግን፣ በጊዜው የኢሕአዴግ መንግሥት የፍትሕ ሥርዓት ላይ እምነት ካጣሁ ቆየሁ፡፡

Abelo #In90Words By Yosef Dagne
He is a well-composed, well-versed man with great humility and courage. He is someone who, once you know him, you realize that he is just the embodiment of the kind of person you always wished to become when you grow up. Any great idea that crossed your mind is as good as done once you discuss it with Abelo. He never gets tired to help anyone in any way he can. As deep as his sense of humor is his focus and attention to the big picture at any moment.
#FreeZone9Bloggers
ስንት ያየሁብሽ ጋዜጣ ሂዎቴ… …ብሎ ማንጎራጎር አሁን ነው። (ከ-ማስረሻ ማሞ)
ተስፋለም ጓደኛዬ እና የሥራ ባልደረባዬ ነው። ጋዜጠኛ ጥራ ስባል ቁጥር አንድ ላይ የማስቀምጠው ተስፍሽን ነው። ተስፍሽን አንድም ቀን "አንተ" ብዬ ጠርቼው አላውቅም። አንተ ብዬ ስጠራው ያራቅኹት ይመስለኛል። በስስት የማየው ታናሽ ወንድሜ ነው። ከጋዜጠኝነት እና ከጸሐፊነት ጋራ ብዙዎች ወደ እስር ቤት ሊላኩ እንደሚችሉ እገምታለሁ፤ መቼም ቀን ግን ወደ እስር ቤት ይሄዳል ብዬ የማላስበው እና በምናቤም የማይመጣልኝ ብቸኛ ሰው ቢኖር ተስፋለም ነው።
ተስፋለም የግል ፖለቲካዊ አመለካከቱ ከጋዜጠኝቱ ጋራ እንዳይጋጭበት የሚጠነቀቅ ወጣት ነው። ለጋዜጠኝነት ከፍ ያለ ክብር እና ዋጋ ይሰጣል። አንዳንዴ እቀናበታለሁ። ስለ ሚዛናዊነት፣ ስለ ተገቢነትና ስለ እውነተኛ ዘገባ አብዝቶ ይጨነቃል። ማንኛውም ዐይነት ዘገባ ከትክክለኛው ወንዝ ተቀድቶ እንዲፈስ ይመኛል፤ ያደርጋል፤ ይጓዛል። መጀመርያ ለሞያው ታማኝ መኾንን ያስቀድማል። ከተስፋለም ጋራ ሳወራ ከታናሽ ወንድሜ ጋራ የማወራ የማይመስለኝ ጊዜ አለ። ኢሕአዴግ እንደ ተስፋለም መስመራቸውን ጠብቀው ለሚሠሩ ሰዎች የማይመለስ አውሬ ይኾናል ብዬ አስቤ አላውቅም። አሁንም መታሰሩን ማመን እውነት አልመስልህ ብሎኛል! የሚሰማኝ፣ እልህ፣ ቁጭት፣ ተስፋ ቢስነትና ቁጣ ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ተስፋለም የማንም ወገን አይደለም። ብቻውን በራሱ የቆመ ጋዜጠኛ ነው። ኢሕአዴግ ተቋም እንደሚፈራ አውቃለሁ። ግሩፕ በእንጭጩ ለመቅጨት የሚያክለው እንደሌለም ይገባኛል። በገለልተኝነት እንደ ተስፋለም የሚቆሙ ጋዜጠኞችንም እንደማይፈልግ የተረዳሁት ግን ዛሬ ነው።
(ከ-ዳኝነት መኮንን) ተስፋለም
Tesfalem Waldyes is the one guy I know who defends the weekly Addis Neger and Fortune in a breath. Amongst us, he is the only one who can dance to the tune of both papers' editorial policy under the big tent of j-school ethics. It is really unfair to jail Tesfish, but who else expects fairness from berket's regime.በቀድሞዉ አዲስ ነገር እና በእስካሁኑ ፎርቱን መካከል ያለውን የርዕዮተዓለም ገደል ማመቻመች ማን እንዳንተ ተስፍሽ!ከዚህ በላይ ጥንቁቅነት፥ ካንተ ወዲያ የጋዜጠኝነት ሚዛናዊነት እና ገለልተኝነት ላሳር!
Tesfalem Waldyes ሁሌም ስለ ጋዜጠኝነት አለባዉያን፣ መሠረታውያን፣ ቀመር፣ እና ሥነ ምግባር አብዝቶ የሚጨነቅ ምናልባትም ብቸኛው ጓደኛችን ነው። ጋዜጠኝነት ማለት accuracy, balance, clarity, and neutrality ከኾነ የማውቀው አንድ ጋዜጠኛ ተሥፋዓለም ወልደየስ ነው። የዜና ዘለላ መቁጠር፣ የፊቸር አለላ ማሰባጠር ማን እንዳንተ ተስፍሽ! ዜናና ታሪክ ሲሠራ ቀዳሚ እና ፊተኛው፤ እስረኞችን ቃሊቲ ሄዶ በመጠየቅ ታታሪው ወንድሜ ጠያቂ እና ስንቅ አሳሪ ያብዛልህ። የእስር ቤት ማስታወሻህን ወይም ደብዳቤህን በናፍቆት እጠብቃለሁ።(ከ-ዳኝነት መኮንን)
ተስፋለም ወልደየስ፦ "ሚዛን" በሳተበት አገር "ሚዛን" ባለ ብዕሩን የተቀማ ጋዜጠኛ (ከዘሪሁን ተስፋዬ)
ሌሊቱ ሊጋመስ ግማሽ ያህል ሰዓት ቀርቶታል። ወትሮም ዓርብ ምሽት ውክቢያ የማያጣው የአዲስ ነገር ቢሮ በግርግር ተሞልቷል። ጋዜጠኛ ወዲህ ወዲያ ይራወጣል። ቀሪው ኮምፒውተር ላይ አፍጥጦ ዘወትር ለሕትመት ዘግይቶ ለሚገባው ጋዜጣ ጽሑፉን ይተይባል። ጋዜጠኛ ተስፋለምም አንዲት ጥጉን ይዞ ይጫጭራል። ዜናዎች ኤዲት ያደርጋል። እኔም ለመጀመሪያ ጊዜ ይዤ የመጣሁትን ዜና ኤዲት እንዲያደረግ ሰጥቼው፤ ወደጀመርኩት የኢኮኖሚ ጽሑፍ ተመለስኩ። ነገር ግን አፍታም ሳይቆይ በንዴት እየቀዘፈ "አሁን በዚህ ሌሊት ይህ ዜና ተብሎ ይሠራል... " ተስፋለም ይህን ይህል ግልጽ ነው። ለሞያው የሚቆረቆር። አንዳች ስህተት መስሎ የሚሰማውን ፊት ለፊት ከመናገር የማይቆጠብ።
ያን ሌሊት በብዙ ጭቅጭቅና ንትርክ ዜናው ተሰርቶ ወጣ። አጋጣሚው ግን ልዩነታችን በጋዜጠኝነት ፍልስፍና ላይ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር። እሱ "ሚዛናዊ" ብሎ የሚሟገትለት ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥራዓት አንዳች የማያራምድ ይልቁንም ጋዜጠኝነትን አሽመድምዶ ልሳን የሚሸብብ መኾኑ ሊያግባባን አልቻለም። እኔ "balanced journalism is a zero-sum game in Ethiopia" ብዬ እሞግተዋለሁ፤ እሱ በየትኛውም የመንግሥት ሥራዓት ቢሆን የጋዜጠኝነት ሕግጋት የማይጣሱ ደንቦች ናቸው ይላል። ይህንንም በሥራው ያሳያል።
ጋዜጠኝነትን ሕይወቱ ያደረገው ተስፋለም፤ በምንም መልኩ ቢሆን ሞያው በትምህርት ቤት ያገኛቸውን የጋዜጠኝነት መርሖዎች እንዲቃረን አይፈልግም። ዜናዎች ሲያዘጋጅ "ሚዛናዊነት" የሚለው መርሕ አለመጣሱን ሲያረጋግጥ ብቻ ነው ወሬው የሕትመት ብርሃን የሚያየው። ይህ ግን በአንዳንድ ባልደረቦቻችን ላይ ጥርጣሬ አልጫረም ማለት አይቻልም። እሱ "ሚዛናዊ" ብሎ የሚጠራው ጋዜጠኝነት፣ ለዘብ የሚል በተለይም አንዳንድ ጠንካራ የሚባሉ ዜናዎችን (በአዲስ ነገር በወቅቱ ዕይታ) አግላይ ነው የሚል ክርክር ይስነሳ ነበር። የዜናዎቹ 'ሚዛን' ለመጠበቅ ሲባል ለዘብተኛ መኾናቸው "ተስፍሽ ለመንግሥት ተቆርቋሪነት ያሳያል" የሚል አንድምታ ያለው ጥርጣሬ ማሳደሩ አልቀረም።
ይሁንና በሚያዘጋጃቸው ዜናዎች ተዓማኒነት፣ ጥራት እና ቋንቋ አጠቃቃም ሁሉም የሚያደንቀው ነበር። በተለይ ማህበራዊ ገጾች ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን እሱ ሳያይቸው እንዲወጡ የሚፈልግ ጋዜጠኛ አልነበረም። የመተረክ ችሎታው፤ የቋንቋ አጠቃቀሙ እና ዝርዝር ጉዳዮችን የማካተት ብቃቱ ልዩ ነው። ተግባቢነቱና ሁለ ገብነቱም የሞያ መርሕ ልዩነት ቢኖርም በሁሉም ዘንድ በፍቅር እንዲፈለግ አድርጎታል። የማይደክም ነው። የእንቅልፍ ሰዓቱ እጅግ በጣም አነስተኛ መሆኑ እንደ ሰው ቆሞ መሄዱ ሁሌም የሚገርመኝ ነው።
ዙረት ይወዳል። በአንድ ሥፍራ መቀመጥ የጋዜጠኛ ተግባር አይደለም ባይ ነው። በመጓዝ ጋዜጠኛ በእውቀት ይበለጽጋል የሚል ዕምነት አለው። ወደ ተለያዩ አገሮች በሚጓዝበት ወቅት ብዙ ጋዜጠኞች የማይሳካላቸውን የጉዞ ማስታዎሻዎችን ማዘጋጀት ላይ የላቀ ብልጫ እንዳለው አሳይቷል። በአንድ ጉዞ ብቻ ለወራት የሚበቃ ታሪክ ይዞ ይመለሳል።
የተስፋለም "ሚዛናዊነት" መርሕ ቢያንስ ቢያንስ ሚዛን የሳቱ አስተዳዳሪዎቻችንን ብትር እንዳይቀምስ ከለላ ይሆነዋል የሚል ዕምነት ነበረኝ። ግምቴ ግን አልሰራም። ሁሌም ጠላት ከጉያው ሥር ካልፈለቀቀ ያስተዳደረ የማይመስለው መንግሥት ተስፋለምን በጠላትነት ፈረጀው። ማዕከላዊ እስር ቤትን ለዜና ሥራ እና እሥረኛ ወዳጆቹን ለመጠየቅ ብቻ የሚሄድበት ጋዜጠኛ፤ አሁን ማደሪያው ኖኗል። እጅግ ልብ የሚሰብር ኢ-ፍትሓዊነት ነው። በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ ይሄን ያህል ለሞያ ታማኝ መሆን የሚያስከፍለው ዋጋ እስር እና እንግልት መሆኑ አሳዛኝ ነው።
የተስፋለም እስር ኢ-ፍትሓዊነት ብቻ አይደለም ጸጸት የሚፈጥረው። ብዙዎቻችን የሥራ ባልደረቦቹ ይህንን እውነታውን ሳንረዳ መቅረታችን ነው። ስለዚህች አገር ተስፋ ነበረው። አዎንታዊ ጉዳዮችን ይበልጥ መፃፍ መንግሥትን ከአውሬነት ወደ ሰለጠነ ሰውነት ይገራዋል የሚል ዕምነት ነበረው። እምነቱ ግን ተስፍሽን ዕራሱን አስከፈለው። ሚዛን የሳተኝ አገር ሕሊና ቢሶች አስተዳዳሪዎች ተሸክማ ተስፋለምን ለአውሊያዋ መገበሪያ አደረገችው። ብዕሩን ነጥቃ ከሚወደው ሞያ ለጊዜውም ቢሆን ለየችው።
ተስፋለምን ከሞያ ባሻገርም እንደ ቅርብ ወንድም እናፍቀዋለሁ። ከነልዩነታችን የጥበብ ፍቅር ያስማማናል። ሁለታችንም ዙረት መውደዳችን በተለያየ አጋጣሚ የተለያዩ ሥራዎች እንድንሰራ አድርጎናል። ከሁሉ ግን ዑጋንዳ ለሥራ ለዓመት በቆየበት ጊዜ የመጀመሪያውን በምስራቅ አፍሪካ የሚሰራጭና በአማርኛ የሚታተም "ሐበሻዊ ቃና" የሚል በስደተኞች ላይ የሚያተኩር ጋዜጣ መጀመሩ ይበልጥ እንደወደው አድርጎኛል- ለሞያውም ጥልቅ ፍቅር እንዳለው መስክሮልኛልና።
ተስፍሽን ባልደረቦቹ በወጉ አልተረዳነውም። ፍቅርና አክብሮታችን ግን ሁሌም ነበር። አሁንም ይበልጥ እንድናከብረው ለሚዛናዊነትም የከፈለውን መስዋዕትነት እንድናስበው ሆኖል። ተስፍሽ ሁሌም የምታከብራት ሚዛናዊነት ከግፈኞች አሳሪዎችህ ነጻ በምትወጣ አገራችን ነፍስ ዘርታ እንደምትላወስ አትጠራጠር። (ዘሪሁን ተስፋዬ)
ለዘጠና ቀናት እስር ዘጠና ቃል ይበቃዋልን… ? ”ስልጣኔንም ሆነ ሰይጣኔን ሊያስለቅቅ የሚተጋ እርሱ አሸባሪ ነው” ኢህአዴግ በአበበ ቶላ ፈይሳ
#in90words
እናስባቸው ዘንድ ዞን ዘጠኞች በእስር ቤት እንደተቆለፈባቸው ዘጠና ቀን የፊታችን ሃሙስ ይሞላቸዋል። በፊት
በማዕከላዊ ያለ ክስ ያለ ፍርድ ታስረው የነበሩት እጅግ ወዳጆቻችን የሆኑት ዞን ዘጠኞች አሁን ከዚህ መልስ ኦነግ
ከዚህ መልስ ግንቦት ሰባት ብዬሃለሁ ብለው የሽብረተኝነት ክስ መስርተውባቸዋል። በአሁኑ ሰዓት ወንዶቹ ቂሊጦ ሴቶቹ
ቃሊቲ ይገኛሉ።
ለመሆኑ እነዚህ ልጆች የምር አሸባሪ ሆነው ነው ያታሰሩትን ብለን የጠየቅን እንደሆነ መለሱ አዎ ነው። ማንን አሸበሩ ብሎ ተከታይ ጥያቄ መጠየቅ ታድያ ተገቢ ነው፤ ማንን አሸበሩ… ያሸበሩት በሆነው ባልሆነው የምተሸበረውን ኢህአዴግ ን ነው። ምን ብለው አሸበሯት ብሎ የሚጠይቅ ካለም ”ህገ መንግስቱ ይከበር” እና ”ሰለሚያገባን እንናገራልን” የሚሉት አቋማቸው ናቸው ኢህአዴግን ያሸበሯት። ድመት የገደለ እጅ ዝም ብሎ ይንቀጠቀጣል እንደሚሉት አባባል ሆኖ እንጂ ሀገ መንግስቱ ይከበር ማለት እና ስለሚያገባን ዝም አንልም እንናገራለን እንገማገማለን ማለት የሚያሸብር ነገር ሆኖ አየደለም ኢህአዴግ ”የተነጰረጰረችው” መንጰርጰር/ ጰርጳራ የምትለው ቃል መነሻዋ የት እንደሆነ ባላውቅም አባቴ እጅግ ለሚፈራ ሰው ይሸልማት የነበረች ቃል ናት።

ጉምቱዋ ኢህአዴግ በአንድ ፍሬዎቹ
ዞን ዘጠኞች ለምን ተንጰረጳረች ብለን የጠየቅን እንደሆነ የመጀመሪያው መላ ምት ”እኛ ሰባት ሆነን ጀመረን የ አስራ
ሰባት አመቱን ደርግ ከደመሰስን እነዚህ ደግሞ ዘጠኝ ሆነው ተደራጅተው ሃያ ዘጠኝ አመት ሳይሞላን በእንጭጩ
ሊያስቀሩን ነው” የሚል ፍርሃት ሊሆን እንደሚችል ይጠረጠራል።
እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ዞን ዘጠኞችን መንግስት ለመደምሰስ ቀርቶ ካሴት ለመደምሰስም ተነሳሽነቱ አልነበራቸውም። ”ስለሚያገባን እንጦምራለን” ማለት ወይም ሀገ መንግስቱ ይከበር ማለት ስልጣን ልቀቁ ማለት አይደለም። እንደ ዞን ዘጠኞች ውትወታ ኢህአዴግ ስልጣን ባይለቅም ሰይጣኑ ከለቀቀው ግድ ያላቸው አይደሉም።
ኢህአዴግስ ምን አለች፤ ያሉ እንደሆነ ስልጣኔንም ሆነ ሰይጣኔን ሊያስለቅቅ የሚተጋ እርሱ አሸባሪ ነው አለች፤
ጰርጳራ በሏት!
እና እላችኋለሁ ዘጠና ቀናት በእስር ያሳልፉትን ዞን ዘጠኞች #in90words ላስባቸው አልኩና አልበቃህ አለኝ፤ ይሄኔም ያንን የአማርኛ ቋንቋ ተማሪ አስታውስኩት፤
መመህሩ እስቲ ሀገራችሁን በስድስት መስመር ግጥም ገለጹ ብሎ የከፍል ስራ ሰጠ፤ ወድያውም አንዱ ተማሪ ጨርሻለሁ አለ፤ እስቲ አንበበው ሲባል፤
እንኳን ስድስት መስመር መቶም አይበቃሽ
እንደው በደፈናው የጉድ ሀገር ነሽ
ብሎ በሁለት መስመር ጨረሰው።
እናም ወዳጆቼ ዞን ዘጠኞች እና ሌሎችም ጋዜጠኞች የሃይማኖት መብት ተከራካሪዎች ፖለቲከኞች እና ያገባኛል ባዮች ሰለ እናነት #in90words ተገለጾ የሚያልቅ ነገር የለም።

#In90Words by Yayyaba Shanan
#In90Words
Though I didn't know #Zone9 bloggers till their detention by the dictator, I used to know them after the hash tag that advocate for their release from prison, controls and dominates the Facebookers' pages & timelines of Ethiopian online community. After that I read some of their updates on their page, which I found national, mature, unbiased & biased, inclusive & ethical, rhetorical with some features of Nostalgia & above all their smart writing style that attracts the readers attention. It is severely painful to see those young national activists facing detention in notorious Woyane's prison.
#In90Words. #FreeZone9Bloggers #FreeJournalists

“ሞንጫሪት” #ዞን9#
ለጋ መሳይ
እጅግ ብስል
ጥልቅ አዋቂ
አፍቃሪ
ተቆርቁዋሪ
ባለ ነገ
ኢሄው ዛሬ
አስጨናቂ
. . . . ነቅናቂ
ትንሽ ሆኖ
ትንሽ መስሎ
የትውልድ ፈርጥ
ፋና ወጊ….!!!!
“ሞንጫሪት” #ዞን9#
እጅግ ብስል
ጥልቅ አዋቂ
አፍቃሪ
ተቆርቁዋሪ
ባለ ነገ
ኢሄው ዛሬ
አስጨናቂ
. . . . ነቅናቂ
ትንሽ ሆኖ
ትንሽ መስሎ
የትውልድ ፈርጥ
ፋና ወጊ….!!!!
“ሞንጫሪት” #ዞን9#
Nati #In90Words by Zerihun Tesfaye
Nati #In90Words
I have known Nati for over five years as an economist, talented social media practitioner and human rights activist. He was too young, the first time I met him, but I observed his passion for politics, economics and civic rights. Since then, his engagement in critical writing and debate on various issues has proved how the young man is really concerned about the poor, and major national issues. He is a critical reader, humble and sociable. He is a terrorist only on the eyes of the authoritarian regime and its supporters.
#FreeZoneNineBloggers

90th
day
On July 24th, it will be exactly 90 days since Zone 9
Bloggers and 3 Journalists were unlawfully arrested.
Want to know more about their arrest?
If you want remember their 90th day, raise your hand!!!
Abel,
Atnaf, Asmamaw, BefeQadu, Edom, Mahlet, Natnail, Tesfalem and Zelalem are
more than brilliant bloggers. They are our friends, our brothers and sisters,
whom we have shared moments and good laughter.
They are our inspiration, the fresh hopes of Ethiopia.
There is a lot we can say about each one of them.
So let’s say it!!!
Since it is 90 days
we invite you to take this opportunity to reflect on how things transpired over the past several weeks.
we invite you to take this opportunity to reflect on how things transpired over the past several weeks.
and why not write a brief note using 90 words?
These could be personal reflections, memories of personal exchanges with the
bloggers & journalists, etc.
How to share?
1.
Post it on your Facebook using #In90Words
2.
Tweet #In90Words and promote the
day
3.
Send your 90 words gratitude to
and we plan to post the note on this website and
please indicate if you want to remain anonymous.
Subscribe to:
Posts (Atom)