“ስለ ሀገራችን ጉዳይ ያገባናል” By Dereje Habtewold

“ስለ ሀገራችን ጉዳይ ያገባናል” በማለታችሁ መታሰራችሁ የሚያመለክተን ነገር ቢኖር፤ አገዛዙ ደንታ- ቢስ ትውልድ ለመፍጠር የተያያዘ ውን የጥፋት ጎዳና ስፋት ነው። “ህገ-መንግስቱ ይከበር!” በማለታችሁ መታሰራችሁ የሚነግረን ሀቅ ቢኖር፣ህግ- መሳሪያችንና የበቀል ዱላችን ሆኖ ይቀጥላል የሚለውን የሹመኞቹን ያልተገራ የፈላጭ ቆራጭነት ምኞት ጥልቀት ነው። “ኑ ኢትዮጵያዊ ህልም እናልም!” በማለታችሁ መታሰራችሁ ፍንትው አድርጎ ያሳየን እውነታ ቢኖር፣ የታሪክ አጋጣሚ በዚች ታላቅ ሀገር ወንበር ላይ ያስቀመጣቸው ስዎች የሰጠሙበትን የጎጠኝነት ኩሬ ርቀት ነው።
በአጠቃላይ መታሰራችሁ ያስረገጠልን ነገር ፦በወንጀለኞች ስርዓት ንፁሀን ዋጋ ይከፍላሉ የሚለውን ሀቅ ነው።
እንኩዋንም አጥፍታችሁ አልታሰራችሁ!
እያንዳንዱዋ ግፍ ዋጋ ሳታስከፍል እንዲሁ አትቀርም። ያበጠው ጎማ የሚተነፍስበት ቀን ይመጣል።

No comments:

Post a Comment