In 90 words


በሚጽፉት ነገር በሁሉም አልስማማም። በአንዳንድ ነገሮች ላይ ከእነሱ የተለየ አቋም ነው ያለኝ። ነገር ግን በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ሕግ አክብረው በሰላማዊ መንገድ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያደርጉ የነበረውን ነገር ሁሉ አከብራለው። ከራሳቸው አልፈው ሁሉም ዜጎች ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብታቸው ተከብሮ በሀገራቸው ጉዳይ የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ በከፈቱት ገጽ ላይ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ነበር። ለሀገራቸው ስለሚያገባቸው በብዕራቸው ሀሳባቸውን ገለጹ። ይሄ አካሄዳቸው በሶሻል ሚዲያ ውስጥ በሚሳተፉ ወጣቶች ላይ መነቃቃትን ፈጠረ። ይሄም በአምባ-ገነኖች ስላልተወደደ" በሽብርተኝነት" ከሰሷቸው። ጋዜጠኞችም ሙያቸውን አክብረው የሚንቀሳቀሱና የሚዘግቡ ስለነበር ለኢህአዴግ አልተመቹትም። ስለዚህ በተለመደው መልኩ አሰራቸው። ለኔ ሁሉም ሰላማዊ ዜጎች፣ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች እንጂ ሽብርተኞች አይደሉም።

Abenezer B. Yisihak

No comments:

Post a Comment