#‎In90Words By Hiwot Wendimagegn

The True Aim of Justice should be to End Crime not to Destroy Lives!!!
Let me just say it upfront, I DETEST Ethiopian politics; I absolutely ABHOR it, I LOATHE it; it’s an utter TRAVESTY!!! As long as history remembers, we have shattered countless lives and killed off each other in the name of political regimes, in the name of “I’m more right than you!!!” LET THE HEARTLESSNESS STOP!!! Ideal youngsters don’t deserve to have their lives destroyed for trying to stand up for a cause much “bigger” than themselves.
የፍትህ ዋና አላማ ጥፋትን ማረቅ እንጂ የሰውን ህይወት ማኮላሸት መሆን የለበትም!!!
ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለኝን ጥላቻ የሚገልጹ ቃላት እስከዛሬ አልተፈጠሩም፣ በማውቃቸው ቃላት የአቅሜን ልሞክርይቀፈኛል፣ ያንገፈግፈኛል፣ ይመረኛል፣ ይከረፋኛል፣ ያንገሸግሸኛል፣ ያሳርረኛል፣ ይገለማኛል፣ ያሳዝነኛል፣ ያቅለሸልሸኛል፣ ተስፋ ያስቆርጠኛል፣ ኢትዮጵያዊነቴን ያስረግመኛል፣ ያመኛልወዘተምነው ይሄን ያህል ? ካላችሁ፣ ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ፣ በስመ ፖለቲካ እና በእኔ የተሻለ አውቃለሁ ሰበብ፣ የስንት ሰዎች ህይወት ተበላሸ፣ የስንት ሰዎች እንባ ፈሰሰ፣ የስንት ሰዎች ህይወት አለፈ!!!… ለፍሬ አልባ ዲስኩር ተጣላን፣ ተጋደልንበቃን አንልም አንዴ?… ከእራሳቸው አልፈው ለሃገር በመቆርቆራቸው፣ የህልመኛ ወጣቶች ህይወት ተሳንክሎ አይቅር! … ይብቃን፣ በደመ ነፍስ፣ በአጭሩ መጓዝ ይብቃን!!!
#In90Words

No comments:

Post a Comment